የግጥም ቤት
ኢትዮጵያ-
ድንቅ ነሽ!
የእራስ ባህል- የ’ራስሽ ልብስ
የእራስ ታሪክ- የ’ራስሽ ቅርስ
የእራስ ቋንቋ- የ’ራስ ፊደል
የእራስ ሐውልት- የራስ ገድል
የ’ራስ የቀን- አቆጣጠር
የ’ራስ የወቅት- አደራደር
የ’ራስ በዓል- አከባበር
ብዙ ቀለም- ብዙ ህብር
ለዘመናት- አንድ በፍቅር
ባዕድ ያልገዛት- ድንግል ምድር
አድባር፣ ገዳም- አብያትሽ
የ’ራስ ጥበብ- የብራና መጻሕፍትሽ
ፍልፍል፣ ውቅር- ድንቃድንቅሽ
የነጭ መንደር- ያልቀላወጥሽ
የ’ራስ አኩሪ- ታሪክ ያለሽ
ኢትዮጵያ- ድንቅ እኮ ነሽ!!!
(መላኩ አ.
ኅዳር 20/2004 ዓ.ም.)
No comments:
Post a Comment