(መላኩ አላምረው)
በመሠረቱ የሰው ልጅ መሰሉን ይበቀል ዘንድ ተፈጥሮው ይፈቅድለታልን? በፍጹም። በቀል የፈጣሪ ነው። ድርሻችንን ለይተን ባለማወቃችን እንጅ የበደሉንን እንበቀል ዘንድ ለእኛ አልተፈቀደልንም። ዓለምን ያበላሻት ድርሻን አለማወቅ ነው ! በፈጣሪ ድርሻ እየገባን ነው የተቸገርነውና መላ ቅጡ የጠፋብን።
ለምሳሌ ሰውን በጥፋቱ ልክ መበቀልና የሥራውን መስጠት የእግዚአብሔር ድርሻ ሆኖ ሳለ እኛ በራሳችን ስሌት ልንበቀል እንሮጣለን። ይህ ግን ሌላ ችግር እንጅ መፍትሔ አያመጣም – ሲያመጣም አላየንም። ምክንያቱም ሰዎች ሰዎችን ስንቀጣ በትክክል በበደላቸው መጠንና አግባብ በሆነ መልኩ አይደለም። ሰው የሰውን በደልም ሆነ መልካምነት ጠንቅቆ የማወቅ ጸጋ የለውም።
ወይ ያጋንነዋል ወይም ያሳንሰዋል። ለዚህም ነው ግፈኞችን መበቀል የሰው ድርሻ ያልሆነው። በማያውቀው መጠን ፍርዱ እየተዛባ ፍትህ እንዳይበላሽ በቀል (ለሰው እንደሥራው መክፈል) የአምላክ እንጅ የሰው ድርሻ አይደለም። ሰው ሰውን ሲበቀል በምድር ሰላም አይወርድም። እርቅና ይቅርታን ሲያደርግ ብቻ ሰው በሰላም ይኖራል።
በመበቃቀል ስሜት ውስጥ ሆነን መካሰስ፣ መፈራረጅ፣ በቡድን መሰዳደብ… አልፎም መገዳደል ለምንፈልገው ነፃነትና ፍትህ አያበቃንም። ያለ እርቅና ይቅርታ የሚቆም ደም፣ የሚመጣም ሰላም እንደሌለ እንመን። ጊዜና ሁኔታ እየጠበቁ በመበቃቀል ዘላቂ ጠላትን እንጅ ነፃነትን ማምጣት የሚቻል እንዳይመስለን።
በቀል ካልተረሳና እርቀ-ሰላም ካልወረደ… እመኑኝ ሀገራችን ለሰው ምቹ መኖሪያ፣ የእኩልነትና የፍትህ ምድር ልትሆን አትችልም። ለችግሮች ሁሉ የሚወሰደው መፍትሔ ጉልበት ከሆነ… ምን አልባት ዛሬ ባለጊዜውና ባለምቹ አጋጣሚው ያሸንፍ ይሆናል። ነገ ደግሞ ታሪክ ይገላበጣል።
ሰዎች በልባቸው በቀልን እስከያዙ ድረስ በአካል ብንጎዳቸውና ብናሸንፋቸው ትርጉም የለውም። የአካል መሸነፍ የመንፈስ መሸነፍንና የልብ ድል መሆንን አያመለክትም። ልብንም መንፈስንም አሸንፎ ሰላም ለመፍጠር ደግሞ ብቸኛው መፍትሔ እርቅና ይቅርታ ነው።

No comments:
Post a Comment