...
ሰሜን ኮሪያ በፕሬዝዳቷ ኪም ጆንግ አንደበት ‹‹የቅርብ ወዳጄ እና ኮሚኒስታዊው
የጦር መሪነት ተምሳሌቴ›› ብላ ለጠራችውና በ90 ዓመቱ ይህችን ዓለም ለተሰናበተው የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ ከኅዳር
19-21/2009 ዓ.ም (እኤአ ከኖቬምበር 28-30/2016) የሚቆይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን አወጀች፡፡
በእነዚህ 3 የሀዘን ቀናት የሰሜን ኮሪያ ሰንደቅ ዓላማ በግማሽ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል፡፡
በእዚህም ሰሜን ኮሪያ ለኩባና እና ላረፉት መሪዋ ያላትን ክብርና አብሮነት ትገልጻለች፡፡
የኩባ እና የሰሜን ኮሪያ ወዳጅነት እኤአ ከ1960 ጀምሮ የተመሠረተና በፖለቲካዊ
ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቶ ሁሉን አቀፍ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይም ከ1968ቱ የካስትሮ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጉብኝት በኋላ
የሁለቱ ሀገራት ኮሚኒስት ፓርቲዎች ፖለቲካዊ ግንኙነት ከዲፕሎማሲ አልፎ ወደ የልብ ከልብ ወዳጅነት እንደተሸጋገረ ይነገራል፡፡
ለዚህም ነው የአሁኑ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም የካስትሮን ሕልፈት ተከትሎ ባፈው እሁድ
ባደረጉት ንግግር፡-
‹‹ፊደል ካስትሮ የቅርብ ወዳጃችን እና ኮሚኒስታዊው የጦር መሪነት ተምሳሌታችን ነበር፡፡
ለሁለቱ ሀገራት ፓርቲዎች፣ ለመንግሥታዊም ሆነ ለሕዝብ ለሕዝብ ግንኙታችን ማደግ ትልቁን ድርሻ የተወጣ ጀግና መሪ ነበር፡፡
ለሀገራችን መልሶ መዋሐድና ጥንካሬም ካስትሮ የተጫወተው ሚና መቼም የሚረሳ አይደለም››
ሲሉ የገለጹት፡፡
‹‹አብዮት ማለት በትናንት እና በነገ (ባለፈውና በመጪው ጊዜ) መካከል እስከ ሞት
ድረስ የሚደረግ ትግል ነው›› - ካስትሮ ከሚታወቁባው ጥቅሶች አንዱ፡፡
ዘገባው የRT.com እና የAFP ነው፡፡
-----//-----
North Korea
declares 3-day mourning for ‘close friend and comrade’ Fidel Castro
...
North
Korea has declared a three-day mourning period for Fidel Castro, who died on
Friday, state media reported, adding that the Cuban leader was the Korean
people’s “close friend and comrade,” who devoted all his life to the prosperity
of his country.
North
Korean flags fly at half-mast in solidarity with Cuba following the death of
Fidel Castro, from November28 till November 30, 2016.
The
mourning was announced on Monday by the official Newspaper of the Central
Committee of the Workers’ Party of Korea.
Earlier
on Sunday, North Korean President Kim Jong-un issued a statement on Castro’s
death, calling him a “close friend and comrade of the Korean people.”
He
“made all efforts to strengthen the friendly and cooperative relations
between the two parties, governments and peoples of our two countries and
extended firm support and encouragement to our efforts for national
reunification and just cause with the invariable revolutionary principle and
obligation for over half a century,” Kim said.
According
to Kim, the revolutionary leader devoted all his life “to the prosperity of
the country and the happiness of the people.”
'A revolution is a struggle to the death between the
future and the past' - Castro’s most
memorable quote.
...
Cuba
has maintained diplomatic relations with North Korea since 1960, with both
nations maintaining embassies in the respective capitals. Castro made an
official visit in 1986.
In
2015, Cuban Vice President Miguel Diaz-Canel met with Kim Jong-un in Pyongyang
on the 55-year anniversary of their diplomatic relations. Also in July of this
year, Kim Jong-un received Salvador Valdes Mesa, one of Cuba’s six vice
presidents.
Source: RT.com
and AFP