Monday, November 28, 2016

ሰሜን ኮሪያ ለፊደል ካስትሮ ሞት የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች ! / North Korea declares 3-day mourning for ‘close friend and comrade’ Fidel Castro



...
ሰሜን ኮሪያ በፕሬዝዳቷ ኪም ጆንግ አንደበት ‹‹የቅርብ ወዳጄ እና ኮሚኒስታዊው የጦር መሪነት ተምሳሌቴ›› ብላ ለጠራችውና በ90 ዓመቱ ይህችን ዓለም ለተሰናበተው የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ ከኅዳር 19-21/2009 ዓ.ም (እኤአ ከኖቬምበር 28-30/2016) የሚቆይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን አወጀች፡፡
በእነዚህ 3 የሀዘን ቀናት የሰሜን ኮሪያ ሰንደቅ ዓላማ በግማሽ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል፡፡ በእዚህም ሰሜን ኮሪያ ለኩባና እና ላረፉት መሪዋ ያላትን ክብርና አብሮነት ትገልጻለች፡፡
የኩባ እና የሰሜን ኮሪያ ወዳጅነት እኤአ ከ1960 ጀምሮ የተመሠረተና በፖለቲካዊ ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቶ ሁሉን አቀፍ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይም ከ1968ቱ የካስትሮ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጉብኝት በኋላ የሁለቱ ሀገራት ኮሚኒስት ፓርቲዎች ፖለቲካዊ ግንኙነት ከዲፕሎማሲ አልፎ ወደ የልብ ከልብ ወዳጅነት እንደተሸጋገረ ይነገራል፡፡
ለዚህም ነው የአሁኑ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም የካስትሮን ሕልፈት ተከትሎ ባፈው እሁድ ባደረጉት ንግግር፡-
‹‹ፊደል ካስትሮ የቅርብ ወዳጃችን እና ኮሚኒስታዊው የጦር መሪነት ተምሳሌታችን ነበር፡፡ ለሁለቱ ሀገራት ፓርቲዎች፣ ለመንግሥታዊም ሆነ ለሕዝብ ለሕዝብ ግንኙታችን ማደግ ትልቁን ድርሻ የተወጣ ጀግና መሪ ነበር፡፡ ለሀገራችን መልሶ መዋሐድና ጥንካሬም ካስትሮ የተጫወተው ሚና መቼም የሚረሳ አይደለም››
ሲሉ የገለጹት፡፡
‹‹አብዮት ማለት በትናንት እና በነገ (ባለፈውና በመጪው ጊዜ) መካከል እስከ ሞት ድረስ የሚደረግ ትግል ነው›› - ካስትሮ ከሚታወቁባው ጥቅሶች አንዱ፡፡
ዘገባው የRT.com እና የAFP ነው፡፡
-----//-----
North Korea declares 3-day mourning for ‘close friend and comrade’ Fidel Castro
...
North Korea has declared a three-day mourning period for Fidel Castro, who died on Friday, state media reported, adding that the Cuban leader was the Korean people’s “close friend and comrade,” who devoted all his life to the prosperity of his country.

North Korean flags fly at half-mast in solidarity with Cuba following the death of Fidel Castro, from November28 till November 30, 2016.
The mourning was announced on Monday by the official Newspaper of the Central Committee of the Workers’ Party of Korea. 
Earlier on Sunday, North Korean President Kim Jong-un issued a statement on Castro’s death, calling him a “close friend and comrade of the Korean people.” 
He “made all efforts to strengthen the friendly and cooperative relations between the two parties, governments and peoples of our two countries and extended firm support and encouragement to our efforts for national reunification and just cause with the invariable revolutionary principle and obligation for over half a century,” Kim said.
According to Kim, the revolutionary leader devoted all his life “to the prosperity of the country and the happiness of the people.”
'A revolution is a struggle to the death between the future and the past' - Castro’s most memorable quote.
...
Cuba has maintained diplomatic relations with North Korea since 1960, with both nations maintaining embassies in the respective capitals. Castro made an official visit in 1986.
In 2015, Cuban Vice President Miguel Diaz-Canel met with Kim Jong-un in Pyongyang on the 55-year anniversary of their diplomatic relations. Also in July of this year, Kim Jong-un received Salvador Valdes Mesa, one of Cuba’s six vice presidents.
Source: RT.com and AFP

No comments: