ትዝታ……
ልክ እንደ ዓባይ ወንዝ ሲሄዱት ቢኖሩ
ልክ እንደ ዓባይ ወንዝ ሲሄዱት ቢኖሩ
እንደ ዋሽንት ዜማ እያንቆረቆሩ
ምንም ቢያጣጥሙት
ምን ቢደጋግሙት
ትዝታ ጥልቅ ነው ከቶ
አይደረስም
ትዝታ ኃያል ነው ከቶ
አይሸነፍም
የማያልፍ ታሪክ የጥንት
ማስታወሻ
የኋልዮሽ መንገድ የትላንት
መድረሻ
ትዝታ ሀሳብ ነው የምንተክዝበት
ትዝታ ስንቅ ነው የምንጽናናበት
ትዝታ ቅጣት ነው ምንጸጸትበት
ትዝታ ደስታ ነው የምንቦርቅበት
ትዝታ ሀዘን ነው የምናለቅስበት
ትዝታ ሕግ ነው የምንቀጣበት
ትዝታ አብሮነት ነው
ትዝታ ባዶነት
ትዝታ ሀብት ነው ትዝታ
ድህነት
ትዝታ እምነት ነው ትዝታ
ክህደት
ትዝታ……..
No comments:
Post a Comment